:::ዜናዎች:::

:::ያግኙን :::

ርዕሰ አንቀጽ

ወጣቱ ወዴት ነው መሄድ ያለበት)
የቤተ ክርስቲያን ታሪክ በሃይማኖት ፍቅር በነደዱ፣ ለተጋድሎ ራሳቸውን በሰጡ የአባቶቻቸውን ታሪክ ለመድገም በቆረጡ ታሪክ ሠሪ ወጣቶች የተሞላ ነው፡፡ እነ አቤልን፣ እነ ይስሐቅን፣ እነ ያዕቆብን፣ ነቢዩ ዳንኤልን እና ሠለስቱ ደቂቅን፣ ባሮክን እና አቤሜሌክን በብሉይ ኪዳን እናገኛቸዋለን፡፡
ተጨማሪ

 
 
  ራእይ
 
የጥያቄዎ መልስ
  ሊቀ ጳጳሱን ይጠይቁ
 
 
 
ገረ ስብከታችን

በኢትዮጵያ ርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በአሜሪካ ለሚቋቋሙ ወይም ለተቋቋሙ አህጉረ ስብከት የተዘጋጀ የመዋቅር ምክረ ሃሳብ

   የሀገረ ስብከቱ ራእይ
   የሀገረ ስብከቱ ተልዕኮ  
   የሀገረ ስብከቱ አወቃቀር 
   የመንበረ ጵጵስና ሀገረ ስብከት ጠቅላላ መንፈሳዊ ጉባኤ
   የሀገረ ስብከት መሥራች ጊዜያዊ ኮሚቴ ሥራ እና መዋቅር 

የሀገረ ስብከቱ ራእይ

በአሜሪካ የሚገኙ አብያተ ክርስቲያናት እና ምእመናን በእምነታቸው ጸንተው፣ በምግባር በርትተው በእናት ቤተ ክርስቲያናቸው መዋቅር ሥር ተጠቃልለው ማየት፤አድባራቱን በማስተባበር ዓለም ሠራዔ መጋቢ እንደሌላት ቆጥረው በዘፈቀደ የሚመላለሱትን በማስተማር እና በማሳመን በክርስትና እምነት ሲመላለሱ ማየት:

የሀገረ ስብከቱ ተልዕኮ           

  • የካህናት መብት እና ግዴታ እንዲጠበቅ ማድረግ 

  • ምእመናን ሃይማኖታቸውን፣ ሥርዓታቸውን፣ ትውፊታቸውንና ባሕላቸውን እንዲያውቁ እና እንዲጸኑ ማድረግ 

  • በአሜሪካ የሚገኙ የልዩ ልዩ እምነት ተከታዮች የኢትዮጵያን ቤተ ክርስቲያን እምነት፣ሥርዓት እና ትውፊት አውቀው እንዲያምኑ እና የቤተ ክርስቲያኒቱ ልጆች እንዲሆኑ ማብቃት 

  • ቤተ ክርስቲያን በአሜሪካ ከታሪኳ እና ከታላቅነቷ ጋር የሚመጣጠን ማኅበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ታሪካዊ ሚና እንዲኖራት ማስቻል 

  • በአሜሪካ የሚገኙ ምእመናን እናት ቤተ ክርስቲያናቸውን በዕውቀታቸው፣ በገንዘባቸው እና በጉልበታቸው የሚያገለግሉበትን መንገድ ማመቻቸት

የሀገረ ስብከቱ አወቃቀር           

ሀገረ ስብከቱ በሊቀ ጳጳስ የሚመራ ሲሆን ከዚህ ቀጥሎ ያሉት አካላት ይኖሩታል  

        የሊቀጳጳሱ ልዩ /ቤት

ሊቀ ጳጳሱን ሐዋርያዊ አገልግሎት ያቀናጃል፣ ዶክመንቶች ይይዛል፣ ለእንግዶች ቀጠሮ ይይዛል፣ የሊቀ ጳጳሱን የመጻጻፍ ሥራዎች ያመቻቻል   

የመንበረ ጵጵስና ሀገረ ስብከት ጠቅላላ መንፈሳዊ ጉባኤ

በቃለ ዐዋዲው ዐንቀጽ 40 መሰረት የሚቋቋምና በዚያም መሠረት ተግባሩን የሚያከናውን ይሆናል  

 ሥራ አስኪያጅ

ሊቀ ጳጳሱ በሌሉበት ጊዜ አስተዳደር ጉባኤውን ይመራል፣የቅዱስ ሲኖዶስ መመሪያዎችን ለሚመለከታቸው ያስተላልፋል፣ የጽ/ቤቱን ሥራ ይመራል፣ ያስተባብራል፣በሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ ሲፈቀድ ሠራተኛ ይቀጥራል፣የሀገረ ስብከቱን የመጻጻፍ ሥራዎች ይሠራል፣ጽ/ቤቱን ወክሎ ከልዩ ልዩ አካላት ጋር ይጻጻፋል፣ የሀገረ ስብከቱን ዕቅድ ከየመምሪያዎች ጋር በመሆን ያዘጋጃል፣አፈጻጸሙንም ይከታተላል፣የሲሦ፣መንፈቀ ዓመት እና የዓመት ሪፖርት ያቀርባል፣

አስተዳደር ጉባኤ

በቃለ ዐዋዲው አንቀጽ 41 መሠረት የሚቋቋም አካል ይሆናል

        የስብከተ ወንጌል እና ሐዋርያዊ አገልግሎት መምሪያ 

ስብከተ ወንጌልን ማስፋፋት፣መምህራንን ማሠልጠን፣መምህራንን መመደብ፣ የማስተማርያ መሣርያዎችን ማዘጋጀት፣ሐዋርያዊ ጉዞዎችን ማዘጋጀት፣ ጉባኤያትን ማቀናጀት ዋና ዋና ተግባራቱ ናቸው  

        የኤኩሜኒካል ግንኙነት መምሪያ

ከሌሎች አኃት አብያተ ክርስቲያናት ጋር የሚኖረውን ግንኙነት ቀና እና የቤተ ክርስቲያኒቱን ሥርዓት እና ክብር የጠበቀ እንዲሆን ማድረግ፣በሥልጠና፣በልምድ ልውውጥ፣በመረጃ፣በመምህራን፣ በአብያተ ክርስቲያናት መካከል መረዳዳት እንዲኖር ማመቻቸት፤ ዋናዋና ተግባራቱ ይሆናሉ               

   የአንድነት ተልዕኮ ማስፈጸሚያ መምሪያ

በእናት ቤተ ክርስቲያን ሥር መሆናቸውን ተቀብለው ነገር ግን ደንባቸው እና አሠራራቸው ያልተስተካከለውን ማስተካከል፤በእናት ቤተ ክርስቲያን መዋቅር ሥር መሆናቸውን ሳይቀበሉ ነገር ግን በገለልተኛነት የቆሙትን አስፈላጊውን የመቀራረቢያ መንገዶች እያዘጋጀ ወደ እናት ቤተ ክርስቲያን የሚመጡበትን መንገድ ማመቻቸት፤ዋና ዋና ተግባራቱ ይሆናሉ

     የወጣቶች ጉዳይ መምሪያ

 ሰንበት ት/ቤቶችን ማደራጀት፣የተደራጁትን በሕገ ቤተ ክርስቲያን መምራት፣ለወጣቶች መንፈሳዊ ሕይወት መጎልበት የሚረዱ ልዩ ልዩ ተግባራትን ማከናወን፣ወጣቶች የሚዘምሩትን መዝሙር ወጥነት እንዲኖረው ማድረግ፣ወጣቶች የቤተ ክርስቲያንን የአብነት ትምህርት ተምረው ወደ ክህነት እንዲቀርቡ ማድረግ፣ዋና ዋና ተግባራቱ ይሆናሉ

   የሕጻናት እና እናቶች ጉዳይ መምሪያ

ለሕጻናት የሚሆኑ ፕሮግራሞችን ማዘጋጀት፤የመማርያ መሣርያዎችን ማዘጋጀት፣ ሕፃናት ሃይማኖታቸውን እንዲማሩ፤የሀገራቸውን ቋንቋ፣ባሕል አውቀው እንዲያድጉ ሁኔታዎችን ማመቻቸት፤እናቶች በቤተ ክርስቲያን አገልግሎት ተገቢውን እንዲፈጽሙ ሁኔታዎችን ማመቻቸት ዋና ዋና ተግባራቱ ናቸው 

    የሕዝብ ግንኙነት እና ሚዲያ መምሪያ

ሬዲዮ፣ቴሌቭዥን፣ጋዜጣ፣መጽሔት ማዘጋጀት፤ ስለ ቤተ ክርስቲያኒቱ የሚመለከታቸው አካላት መግለጫ እንዲሰጡ መንገድ ማመቻቸት፤ ቤተ ክርስቲያንን የተመለከቱ ጉዳዮችን መከታተል፤ መልስ ለሚያስፈልጋቸው ጉዳዮች መልስ ማዘጋጀት፤ ቤተ ክርስቲያንን በተመለከተ ጥያቄዎች ወይንም ሃሳቦችን ይዘው ለሚመጡትን ማስተናገድ ዋናዋና ተግባራቱ ይሆናሉ 

      የፋይናንስ እና አስተዳደር ጉዳዮች መምሪያ

የገንዘብ አወጣጥን እና አገባብን መከታተል፤ የአብያተ ክርስቲያናትን መዋጮ መሰብሰብ፣የገቢ መንገዶችን መተለም፤ ከክህነት አገልግሎት ውጭ ያለውን የሰው ኃይል ምደባ እና አስተዳደርን ማከናወን፣ክፍያዎችን መፈጸም፣የንብረት አስተዳደርን ማከናወን ዋና ዋና ተግባራቱ ናቸው     

        የታሪክ እና ባሕል ጉዳዮች መምሪያ

ዐውደ ርእይ ማዘጋጀት፣ቋሚ ዐውደ ርእይ መክፈት፣ጎብኝዎች ኢትዮጵያን እና ቤተ ክርስቲያንን እንዲጎበኙ ማበረታታት እና መንገድ ማመቻቸት፣ የየአብያተ ክርስቲያናቱ ታሪክ እና ቅርስ እንዲመዘገብ እና እንዲጠበቅ ማድረግ፤ዓመታዊ በዓላትን፣ፌስቲቫሎችን ፣እና ሌሎች ባሕላዊ ዝግጅቶችን ማዘጋጀት

      የሕግ መምሪያ  

ቤተ ክርስቲያንን በተመለከተ ለሚነሡ የሕግ ጉዳዮች አስፈላጊውን ማከናወን፤ ቤተ ክርስቲያን በሕግ መብቷ እንዲጠበቅ ማድረግ፣ የቤተ ክርስቲያን ደንቦች እና ሕጎችን ከሀገሩ ሕጎች ጋር ማጣጣም

ይህ መዋቅር ተግባራዊ ሆኖ ሀገረ ስብከቱ የራሱ ቢሮ እና መንበረ ጵጵስና ይኖረው ዘንድ መሥራች ኮሚቴ ተቋቁሟል

የሀገረ ስብከት መሥራች ጊዜያዊ ኮሚቴ ሥራ እና መዋቅር 

ራእይ

ሀገረ ስብከቱ ተመሥርቶ እና ተገቢው የሰው ኃይል፣በጀት እና ማቴርያል ተሟልቶ አገልግሎቱን ሲፈጽም ማየት

ተልዕኮ

        የሀገረ ስብከቱን /ቤት፣ መንበረ ጵጵስና እና አጥቢያ ቤተ ክርስቲያን መቋቋም

        ተገቢ የሆነውን የሰው ኃይል እና መሣርያ መሟላት

        ለቋሚው መዋቅር ሥራውን ማስረከብ

በዚህ ጉዳይ አስተያየት ፣ሀሳብ፣ማሻሻያ ወይንም ደግሞ ጥያቄ ካለዎት

በስልክ ቁጥር  571 435 0196 ደውለው ማግኘት ይችላሉ፡፡

  Listen Lesson of the week
  Listen Mesbak of the week
  Downlad Songs and Publications
  Discover Ethiopian Orthodox Church History
  Preaching of the week
 
  www.eotc-mkidusan.org
 
www.mahiberekidusan.org
  www.radiotewahedo.org
  www.tewahedomedia.org
Home| Feedback| Webmaster
EOTC-DC Diocese., All Rights Reserved