:::ዜናዎች:::

:::ያግኙን :::

ርዕሰ አንቀጽ

ወጣቱ ወዴት ነው መሄድ ያለበት)
የቤተ ክርስቲያን ታሪክ በሃይማኖት ፍቅር በነደዱ፣ ለተጋድሎ ራሳቸውን በሰጡ የአባቶቻቸውን ታሪክ ለመድገም በቆረጡ ታሪክ ሠሪ ወጣቶች የተሞላ ነው፡፡ እነ አቤልን፣ እነ ይስሐቅን፣ እነ ያዕቆብን፣ ነቢዩ ዳንኤልን እና ሠለስቱ ደቂቅን፣ ባሮክን እና አቤሜሌክን በብሉይ ኪዳን እናገኛቸዋለን፡፡
ተጨማሪ

 
 
  ራእይ
 
የጥያቄዎ መልስ
  ሊቀ ጳጳሱን ይጠይቁ
 
 
 

የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት ምን ለምን እንዴት

  

የሰንበት ት/ቤቶች አንድነትና የአንድነት ፍሬ በተለያዩ አጋጣሚዎች ታይቷል፡፡ይሁን እንጂ አንድነቱ የተጠናከረ ባለመሆኑ የተከሰቱ ችግሮችም አሉ፡፡ ለአንድነቱ መላላት ምክንያት የሆኑቱን በሁለት ከፍሎ መመልከት መልካም ነው ፡፡እነርሱም ዉጫዊና ዉስጣዊ ችግሮች ናችዉ፡፡        

ዉጫዊ ቸግሮች

        መናፍቃን በሰንበት ት/ቤቶች መካከል በሚነዙት አሉባልታ የሚፈጠረዉ
      መራራቅ

        የሰንበት ት/ቤቶችን ዓላማ ባለመረዳትና በምግባረ ብልሹ ተማሪዎች የተነሳ
      የሚፈጠረዉ የተሳሳተ አመለካከት

        የሚመለከታቸዉ አንዳንድ የቤተ ክርስቲያን ክፍሎች በየአህጉረ ስብከቱ
      ለሰንበት ት/ቤቶች መጠናከር የሚያደርጉት ድጋፍ አነስተኛ መሆን

    

ዉስጣዊ ችሮች

    የሰንበት ት/ቤትን ዓላማ በትክክል አለመረዳት

    የአንዳንድ ሰንበት ት/ቤቶች ለራሳቸዉ ጉዳይ ቀስቃሽ/ጋባዥ/ መጠበቅ

    የራስን ሰንበት ት/ቤት አንዳንዴም ግለሰባዊ ዝናን መፈለግና ከሌሎች ጋር
       ለመሥራት ያለመፈለግ

    የአቅም ማነስ

    የሰንበት ት/ቤቶችን አንድነት ዓላማና ጥቅም ያለመገንዘብና የሚገባዉን
       ያለመሥራት

    ከመደማመጥና ከመወያየት ይልቅ የአንድን ሰንበት ት/ቤት /ግለሰብ/ ሐሳብ
       ብቻ እንዳይፈጸም መሞከር

    ተቀራርቦ ካለመሥራት የተነሳ ከኑፋቄ ለመጠበቅ በሚል እርስ በርስ
       አለመተማመን ወዘተ ናቸዉ፡፡ 

በአጭሩ የዘረዘርናቸዉን ምክንያቶች በጊዜዉ መፍትሔ ከሰጠናቸዉ የአንድነታችን መጠናከር እዉን ሊሆን ይችላል፡፡ ይህ እንዲሆን ግን ሰንበት ት/ቤቶች ዓላማዉን ተረድተዉ ለተግባራዊነቱ መንቀሳቀሰቀ ይጠበቅቸዋል፡፡ 

እስከአሁን በአንድነት የተሠራዉ ሥራ የሚናቅ አይደለም፡፡ ነገር ግን በ #አንድነት$ ስም የኑፋቄ መርዝ የተረጨበት ሁኔታ እንደነበር አንዘነጋም፡፡ ስለዚህም ሰንበት ት/ቤቶች በመጀመሪያ ራሳቸዉን ኑፋቄ ከሚዘሩ አካላት መጠበቅ ከዚያም በአንድነቱ ጉዞ ውስጥ በጥንቃቄ መመላለስ ይገባቸዋል፡፡ በዚህ ረገድ አብያተ ክርስቲያናት እያንዳንዱን ሰንበት ት/ቤት ከኑፋቄ የተጠበቀ መሆኑንና የአንድነቱም ሂደት በመናፍቃን እንዳይሰናከል በመከታተል ትልቅ ሚና ሊኖራቸው ይገባል፡፡  

የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት ይጠንክር ሲባል አስቀድሞ የአንድነቱን ጥቅምና መገለጫዎቹን በሚገባ መለየት ያስፈልጋል፡፡ በመጀመሪያ የእያንዳንዱ ሰንበት ት/ቤት መጠናከር ለጠቅላላው አንድነት መጎልበት ወሳኝ ድርሻ አለውና የሰንበት ት/ቤቶች መጠናከር ትኩረት ሊሰጠው ይገባል፡፡ ሁሉም ሰንበት ት/ቤቶች ተመሳሳይ ዕድገትና የአደረጃጀት ደረጃ ይኑራቸው ማለት የሚያስቸግር ቢሆንም ዕድገታቸው መቀራረብ ግን ይኖርበታል፡፡ 

ቀደም ብለን የጠቀስነው እንዳለ ሆኖ የእያንዳንዱ ሰንበት ት/ቤት መጠናከር ብቻ የሩጫው መጨረሻ  ሊሆን አይችልም፡፡ የበለጠ አገልግሎት ለመስጠት አንድነት ያስፈልጋል፡፡ የእጅ ጣቶቻችንን በየራሳቸው ሙሉ ናው፤ ዕቃ ለማንሳት ግን አንድነት መሆን አለባቸው፡፡  

የሰንበት ት/ቤች አንድነት ለቤተ ክርስቲያን የሚሰጠው ጥቅም ብዙ ነው፡፡ ጥቂቶቹን እንደሚከተለው አቅርበናቸዋል፡፡

 

ሀ. ዐቅምን ለማስተባበር 

በየትም ቦታ ያሉ ሰንበት ት/ቤቶች በተናጠል ለቤተ ክርስቲያን በመስጠት ላይ ያሉት አገልግሎት ከፍተኛ ነው፡፡ ለዚህም ነው የሰንበት ት/ቤቶች ተሳትፎ በሁሉም መድረክ የሚታየው፡፡ ይህ አስፈላጊነታቸውም የመነጨው አባሎቻቸው በጉልበታቸው፤ በዕውቀታቸውና በገንዘባቸው ከሚያደርጉት አስተዋጽዖ ነው፡፡ 

እንግዲህ ሰንበት ት/ቤቶቹ ያላቸውን ኃይል በማስተባበር ቢንቀሳቀሱ ለቤተ ክርስቲያን እስከ አሁን ከሠሩት የበለጠ ጠቃሚ አገልግሎት ማበርከት እንደሚችሉ መገመት አያዳግትም፡፡ አንድነታቸው የቤተ ክርስቲያንን ችግሮች በማቃለሉም ረገድ ከፍተኛ ሚና ይኖረዋል፡፡ #ድር ቢያብር አንበሳ ያሥር$ ነውና ከነተረቱ፡፡ በየሰንበት ት/ቤቱ ያለው አቅም ቢቀናጅ የሚሠራው ሥራ ሊኖር አይችልም፡፡ 

የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት መፍጠር ዐቅማቸውን ለማስተባበር ስለሚረዳቸውም በኅብረተሰቡ ውስጥ ሰንበት ት/ቤቶች /ቤተ ክርስቲያን/ የሚኖራቸውን ተሳትፎ ያሳድጋል፡፡ 

ለ ሥርዓተ ቤተክርስቲያንን ለመጠበቅ 

የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያንን ተባብሮ ለመጠበቅ እና ለማስጠበቅ ይረዳል፡፡ ቀላል ከሚመስሉን ከምንዘምራቸው መዝሙሮች ይዘትና ዜማ መለያየት እንኳን ብንጀምር ተቀራርበን መወያየቱ ከሚሰሙት ቅሬታዎች ያድነን ነበር፡፡ የትምህርት አሰጣጥ፤ የሥነ ጽሑፍና የድራማ መልእክቶችና አቀራረባቸው እንዲሁም አሁን ሽብሸባችን ጭምር እየተለያየ መጥቷልና አንድነታችን እነዚህንና ሌሎችንም ችግሮችን ለማስወገድ ይረዳናል፡፡ 

የተጠቀሱትና ሌሎችም ችግች ዛሬ በመቀራረብ ካልተስተካከሉ ነገ ለማረም እንደሚያስቸግሩ ከወዲሁ መታወቅ አለበት፡፡ ስለዚህም የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት መጠናከሩ አስፈላጊ ነው፡፡ 

ሐ. ልምድ ለመለዋወጥ 

የሰንበት ት/ቤቶችን ዕድገት አዝጋሚ ካደረጉት ምክንያቶች ዋነኛው የልምድ አለመለዋወጥ ነው፡፡ አዳዲስ ሰንበት ት/ቤቶች ከቀደምቶቹ ስህተትም ሆነ ጠንካራ ጎን የሚማሩበት አጋጣሚ በጣም አነስተኛ ነው ማለት ይቻላል፡፡ ስለዚህም ቀደምቶቹ የሠሩትን ስህተት እየደገሙ መጓዝ ግድ ሆኖባቸዋል፡፡ 

ከመድረክ ዝግጅት ጀምሮ እስከ ኮሚቴ አወቃቀርና አሠራር በአንዱ ሰንበት ት/ቤት የተሠራው ስህተት በሌላውም ይደገማል፡፡ ቀደምት የሚባሉትም የግድ እነሱ በሄዱበት መንገድ ሌሎችም መሄድ ያለባቸው ይመስል #እኛም ዘንድ ይህ ችግር ነበረ$ ከማለት አልፈው ልምዳቸውን ሲያጋሩ አይታዩም፡፡ አዲስ የሚባሉትም በትሕትና ከሌሎች ጥንካሬና ድክመት ለመማር ከመጠየቅ ይልቅ በራሳቸው አመለካከትና ብዙም የማያራምድ ልምድ መመካትን ያዘወትራሉ፡፡ ቀደምቱን አስተምሩን ምከሩን ማለት አላዋቂነት ይመስላቸዋል፡፡ 

ልምድ መለዋወጥ ሲባል የግድ አዲሱ ከቀደሙት ማለት ብቻም አይደለም፡፡ ቀደምቱ ከአዲሶቹ የሚማሩት ነገር ብዙ ነው፡፡ ከተመሠረቱ ረዘም ያለ ጊዜ የሆናቸው አንዳንድ ሰንበት ት/ቤቶች ከሌሎች ሰንበት ት/ቤቶች ጋር ያላቸው ግንኙነት በ #ማስተማር$ ወይም ልምድን በማካፈል ላይ ብቻ የተመሠረተ እንዲሆን ይሻሉ፡፡ ለዚህም ይመስላል ዕድሜያቸዉና ዕድገታቸው አራምባና ቆቦ የሆነው፡፡ 

ሰንበት ት/ቤቶቻችን በሁሉም ዘርፍ ልምዳቸውን መለዋወጥ፤ ከአንዱ ስሕተት ሌላው መማርና መተራረም አብረውም ማደግ ይኖርባቸዋል፡፡ ለአንድ ዓላማ መቆም የሚቻለውም ተመሳሳይ አካሔድ/ርምጃ/ ሲኖር ነው፡፡ ይህም ይሆን ዘንድ የአንድነቱ መጠናከር ወሳኝ ይሆናል፡፡ 

ብዙ የሰንበት ት/ቤት ተማሪዎች #አንድነት$ ሲባል በምን ሊገለጽ እንደሚችል ግራ ሲገባቸው ይታያል፡፡ በየደብራቸው የሚያደርጉት ዝግጅት መኖር፤ በሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን ማስተማራቸውና ኮርስ መስጠታቸው ብቻ የአንድነታቸው መገለጫዎች ይመስላቸዋል፡፡ ጉዳዩ ከዚህ ሰፋ ያለ ነው፡፡ ለቀጣይ የሰንበት ትምህርት ቤቶቻችን እንቅስቃሴ ቢያንስ አቅጣጫ ያመለክታሉ ያልናቸውን እንደሚከተለው አቅርበናቸዋል፡፡ 

ሀ. መንፈሳዊ ጉባኤዎችን በማዘጋጀት፡- 

ሰንበት ት/ቤቶች በየሳምንቱ በየደብራቸው ከሚያደርጉት መርሐ ግብር በተጨማሪ እንደ ጊዜው አመቺነት የተወሰነ ወቅት በአንድነት የሚያዘጇቸው ጉባኤያት ቢኖሩ ከፍተኛ ጥቅም ያስገኛሉ፡፡ 

ከትንሹ ለመጀመር ጉባኤያትን ለማዘጋጀት በአንድ አካባቢ ባሉ ሰንበት ት/ቤቶች ደረጃ ቢጀመር ሥራውን ቀና ሊያደርገው ይችላል፡፡ ለምሳሌ በየሦስት ወር ጉባኤ ቢኖራችው በዓመት አራት ጉባዔ ይኖራቸዋል ማለት ነው፡፡ ከዚያ ከፍ ብሎ በሀገረ ስብከት ደረጃ በዓመት ሁለት ጊዜ በአንድነት በሁሉም ተሳትፎ የሚዘጋጁ ጉባኤያት ቢኖሩ ለአንድነቱ መጎልበት አስተዋጽዖ ያደርጋል፡፡ 

ይህ አጋጣሚ ለመንፈሳዊ ሕይወትና ለአንድነቱ ስሜት መፍጠር ከመርዳቱ በተጨማሪ ሰንበት ተማሪዎች እርስ በርስ እንዲተዋወቁ ያደርጋል፡፡ የልምድ መለዋወጫ አጋጣሚ መሆኑም አያጠያይቅም ፡፡

ለ. የውይይት መድረኮችን በመፍጠር፡- 

ከመንፈሳዊ ትምህርት በተጨማሪ ስለ ሰንበት ት/ቤቶች ችግሮችና መፍትሔያቸው፤ ስለ አሠራርና አወቃቀራቸው፤ ስለ ወቅታዊ ሁኔታዎችወዘተ የሚነጋገሩበት /የሚወያዩበት/ ጉባኤ ሊዘጋጅ ይገባል፡፡ 

በውይይትና በጥናታዊ ጉባኤዎቻቸንም ላይ በሚገባ የተጠኑ የመፍትሔ ሐሳብን የሚያመላክቱ ጥናቶች እንዲቀርቡ ሰንበት ት/ቤቶች የዐቅማቸውን መሞከር አለባቸው፡፡ 

ሐ. ትምህርታዊ ጉብኝቶችን በማድረግ፡- 

በአሁኑ ወቅት በሰንበት ት/ቤቶቻችን መካከል የአሠራር ልዩነት እንዳለ ይታወቃል፡፡ በርግጥ መሠረታዊ ከሆኑ ጉዳዮች ሌላ የግድ አንድ ዓይነት አሠራር ይኑር ማለት ያስቸግራል፡፡ ምክንያቱም የአሠራር ዘዴው የየሰንበት ት/ቤቶቹን የሰው ኃይል፤ልምድና ዐቅም ይጠይቃልና ነው፡፡ 

በአጠቃላይ ግን ታሪካዊ ቦታዎችን ሁሉ ቢያንስ በአቅራቢያችን ያሉ ሰንበት ት/ቤቶችን እንቅስቃሴና አሠራር የመጎብኘት ልምድ ቢኖር ብዙ መማማር ይቻላል፡፡ ጉብኝቱ ቀልጣፋ እንዲሆንም በአገልግሎቱ /በኮሚቴዎች ውስጥ/ የሚሳተፉትን ብቻ በመምርጥ ትምህርታዊ ጉብኝት ማድረግ ይቻላል፡፡ ተጎብኝው ሰንበት ትምህርት ቤትም ድክመቱን ሳይሸፍን በጎውንም ሳያጋንን ማሳየትና በችግሮቹ ላይ መወያየትና መፍትሔ መፈለግ ይገባል፡፡ የአንዱ ሕመም የሌላውም ሆኖ መድኃኒቱን በአንድነት መሻት ስንጀምር እውነትም #አንድ ነን$ ማለት ይቻላልና ሰንበት ት/ቤቶች ቢያስቡበት፡፡ 

መ. ዝግጅትን መለዋወጥ 

የአንዱ ሰንበት ት/ቤት የተወሰኑ አባላት ወደሌላ ሰንበት ት/ቤት ሄደው ዝግጅቶቻቸውን፤ ትምህርት፤ መዝሙር፤ ሥነ ጽሑፍ፤ድራማቢያቀርቡ መልካም ልምድ የመለዋወጫ አጋጣሚ እንደሚሆን ይታመናል፡፡ 

የዚህ ግንኙነት መፈጠር ዋና ዓላማ ልምድ መለዋወጥ ነውና ግንኙነቱን በወንድማማችነት መንፈስ መፈጸም እንደሚገባ መረሳት የለበትም፡፡ በየራሳችን መርሐ ግብሮች ላይ የምናሳየውን ቅንጅትና አቀራረብ ተጋብዘን በምንሄድበት ብቻ የምናይ ከሆነ የምናገኘው ጥቅም አይኖርም፡፡ ለምን ቢባል ፍጹማን መስለን ቀርበናልና፡፡ ስለዚህም የመተራረሚያ መድረኩን ወደ አላስፈላጊ ውድድር እንዳንወስደው ልንጠነቀቅ ይገባል፡፡ ዝግጅቶቻችንንም ካቀረብን በኋላ መወያየት አስተያየት መስጠትና መቀበል ከቻልን ወደ ግባችን ሊያደርሰን ይችላል፡፡ 

አንድነቱ በአንድ ጀንበር የሚመጣ አይደለምና ሰንበት ት/ቤቶች ከሚመለከታቸው ክፍሎች፤ ከአባቶች እና እርስ በርስ መቀራረብና መወያት ይኖርባቸዋል፤ በመደማመጥ በትዕግሥተና በትጋት መሥራት ይገባል እንላለን፡፡