:::ዜናዎች:::

:::ያግኙን :::

ርዕሰ አንቀጽ

ወጣቱ ወዴት ነው መሄድ ያለበት)
የቤተ ክርስቲያን ታሪክ በሃይማኖት ፍቅር በነደዱ፣ ለተጋድሎ ራሳቸውን በሰጡ የአባቶቻቸውን ታሪክ ለመድገም በቆረጡ ታሪክ ሠሪ ወጣቶች የተሞላ ነው፡፡ እነ አቤልን፣ እነ ይስሐቅን፣ እነ ያዕቆብን፣ ነቢዩ ዳንኤልን እና ሠለስቱ ደቂቅን፣ ባሮክን እና አቤሜሌክን በብሉይ ኪዳን እናገኛቸዋለን፡፡
ተጨማሪ

 
 
  ራእይ
 
የጥያቄዎ መልስ
  ሊቀ ጳጳሱን ይጠይቁ
 
 

ከሻኩራው ሰንማር

 ካህኑ መሥዋዕተ ዕጣኑን በሚያቀርብበት በጽንሐሑ ሦስት ገመዶች ላይ ተንጠልጥለው የሿሿቴ ድምፅ የሚያሰሙት ክብ ቅርጾች ሻኩራ ይባላሉ፡፡ ሦስቱ የብረት ገመዶች የሥላሴ ምሳሌ ሲሆኑ ገመዶቹ ከላይ አንድ መሆናቸው የአንድነታቸው ምሳሌ ነው፡፡ እነዚህ ሻኩራዎች አጠቃላይ ቆጥራቸው 24 ነው፡፡ ይህም ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ እያሉ ያለማቋረጥ የሚያመሰግኑት የካህናተ ሰማይ የሱራፌል ምሳሌዎች ናቸው፡፡

እነዚህ ሻኩራዎች በብረት ገመዱ ላይ ሆነው ካልሆነ በስተቀር በየራሳቸው አገልግሎት አይኖራቸውም፡፡ ምሳሌነታቸውም አይገለጥም፡፡ ድምፃቸውም ኅብር እና ክብር አይኖረውም፡፡ አገልግሎታቸውም ቤተ ክርስቲያናዊ መሆኑ ይቀራል፡፡ አንዱ ሻኩራ ከሌሎቹ 23 ጋር አንድ ሆኖ ሲጮኽ፣ አንድ ሆኖ ሲታጠንበት፣ አንድ ሆኖ ሲያገለግል ብቻ አገልግሎቱም ድምፁም ፍሬያማ ይሆንለታል፡፡

የቤተ ክርስቲያን አገልግሎትም እንዲሁ ነው፡፡ ወንድሞች በኅብረት ቢቀመጡ እነሆ መልካም ነው እነሆም ያማረ ነው /መዝ.1321/ በማለት ቅዱስ ዳዊት አስቀድሞ በብሉይ ኪዳን መሰባሰባችንን አንተው /ዕብራ.1024/ በማለት ቅዱስ ጳውሎስ በሐዲስ ኪዳን እንዳስተማሩን እያንዳንዱ አገልጋይ ከሌላው አገልጋይ፤ እያንዳንዱ አገልጋይም ከግንዷ ከቤተ ክርስቲያን ከተነጠለ አገልግሎቱ ፍሬያማ አይሆንም፡፡

አንዲቱ አጥቢያ፣ አንዱ ካህን፣ አንዱ ምእመን፣ አንዱ ሰንበት ትምህርት ቤት ሕልውናው የሚታወቀው ከሌሎች ጋር ኅብረት አንድነት ከኖረው ብቻ ነው፡፡ ሻኩራው ኅብረቱን የሚያገኘው ከተንጠለጠለበት ከብረት ገመዱ ነው፡፡ ሁሉንም ሻኩራ የሚይዘው እርሱ ነው፡፡

አገልጋዮችም፣አጥቢያዎችም፣ ማኅበራትም ኅብረታቸውን ሊያገኙት የሚችሉት በራሳቸው ሳይሆን እንደ መልካም የወይን ዘለላ ከምትሸከማቸው ግንድ ከቤተ ክርስቲያን ነው፡፡ ቤተ ክርስቲያን ራስዋ ክርስቶስ እርሷም አካሉ ናትና፡፡

ጌታችን ስለ ወይን ግንድ እና ፍሬ ባስተማረበት አንቀጽ የግንዱን እና የቅርንጫፉን ግንኙነት ሲያስረዳን ቅርንጫፍ በወይኑ ግንድ ባይኖር ከራሱ ፍሬ ሊያፈራ እንዳይቻለው እንዲሁ እናንተ ደግሞ በእኔ ባትኖሩ ትችሉም፡፡ እኔ የወይን ግንድ ነኝ፡፡ እናንተም ቅርንጫፎች ናችሁ ብሎናል /ዮሐ.154/::

አንዱ ሻኩራ ለብቻው ከግንዱ ተነጥሎ የሚያደርገው አገልግሎትም ሆነ ጩኸት ቤተ ክርስቲያናዊ እንደማይሆነው ሁሉ አገልጋዮችም ሆኑ አጥቢያዎች በአንዲቱ ቤተ ክርስቲያን አማካኝነት ኅብረት አንድነት ፈጥረው ካልጮኹ ካላገለገሉ በቀር አገልግሎታቸው ግላዊ እንጂ ቤተ ክርስቲያናዊ ለመሆን አይችልም፡፡

አባቶቻችን በካህናት እጅ መሥዋዕተ ዕጣን የሚቀርብበትን ጽንሐሕ በቅዳሴም ሆነ በሌሎች ጸሎቶች ጊዜ አገልግሎት ላይ እንዲውል እና ለእይታችን ቅርብ እንዲሆን ካደረጉባቸው ምክንያቶች አንዱ አንድነታችንን አዘውትረን ማሰብ እንድንችል እና ስለ አንድነታችንም እንድንጸልይ ነው፡፡ እኛ ወይም አጥቢያችን በጽንሐሑ ላይ እንደሚገኙት ሻኩራዎች ነን፡፡ ከግንዱ ከተነጠልን እንወድቃለን፡፡

ስለዚህም ፈሬ ለማፍራት እንድንችል እንደ ሻኩራዎቹ በአንድነት እናገልግል፡፡

Home| Feedback| Webmaster
EOTC-DC Diocese., All Rights Reserved