:::ዜናዎች:::

:::ያግኙን :::

ርዕሰ አንቀጽ

ወጣቱ ወዴት ነው መሄድ ያለበት)
የቤተ ክርስቲያን ታሪክ በሃይማኖት ፍቅር በነደዱ፣ ለተጋድሎ ራሳቸውን በሰጡ የአባቶቻቸውን ታሪክ ለመድገም በቆረጡ ታሪክ ሠሪ ወጣቶች የተሞላ ነው፡፡ እነ አቤልን፣ እነ ይስሐቅን፣ እነ ያዕቆብን፣ ነቢዩ ዳንኤልን እና ሠለስቱ ደቂቅን፣ ባሮክን እና አቤሜሌክን በብሉይ ኪዳን እናገኛቸዋለን፡፡
ተጨማሪ

 
 
  ራእይ
 
የጥያቄዎ መልስ
  ሊቀ ጳጳሱን ይጠይቁ
 
 

የኒዉዮርክ ቅድስት ሥላሴ ቤተ ክርስቲያን መንበረ ጵጵስና አመሠራረት ታሪክ

አባ አብርሃም
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን

የሰሜን ምሥራቅ የደቡብ ምሥራቅና የመካከለኛው አሜሪካ

 የኒውዮርክ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ

ተዘክር መዋዕለ ትካት ወለቡ ዓመተ ትዉልደ ትዉልድ 
ተሰአሎ ለአቡከ ወይነግረከ ወለአእሩጊከ ወይዜንዉከ
የድሮዉን ዘመን አስብ፤
የልጅ ልጅንም ዓመታት አስተዉል፤
አባትህን ጠይቅ ይነግርህማል፤
ሽማግሌዎችህን ጠይቅ ይተርኩልህማል።
ዘዳግም ፴፪ ፡፯ _፰

ታሪክ ታማኝነትን እዉነትን ሊያጨስብጥና ሊያስዳስስ የሚችለዉ ቅዱሳት መጻሕፍት እንደሚነግሩን የጥንቱን ዘመን በማሰብ፣ ዓለም ከተፈጠረ ዘመን ከተቆጠረ ጀምሮ ከአበዉ ወደ ልጅ ልጅ የተሸጋገሩትን ዘመናት ወደ ኋላ መለስ ብሎ በዐይነ ሕሊና በማየትና በመቃኘት ከአባት ጠይቆ በመረዳት ከሽማግሌዎች ጠይቆ እዉነተኛ ታሪክን በመያዝ ነው፡፡ ይኼውም ከነበረዉ ተነሥቶ የነበረዉን ጠብቆና አክብሮ በመጠቀምና ትዉልድ እንዲጠቀምበት ስርዝ ድልዝ የሌለዉን በልብ ወለድና በፈጠራ ያልተበከለዉን ከሥጋዊ ምኞትና ከጊዜያዊ የዓይን አምሮት በመነጨ ስሜት ትናንት የማይባልለትን፣ የታሪኩን ባለቤት ወደ ጎን በመተው ባለ ታሪክ መሆን የበደል በደል መሆኑን የታሪክ ባለ አደራ የሆነዉ ትዉልድ ታሪኩን ይጠብቅ ዘንድ ታሪኩን ከየሚመለከታቸዉ ክፍሎች በመጠየቅና በማጥናት አደራዉን እንዲወጣ የብዙ ትዉልድንም ዓመታት አስተዉል ይላል፡፡ 

ስለሆነም በሰሜን አሜሪካ ለቤተ ክርስቲያናችን ከታሪኳ አንዱ የሆነዉን የመጀመሪያዉን ቤተ ክርስቲያን ታሪክ ከሞላ ጎደል ከረጅሙ በአጭሩ ከብዙ በጥቂቱ ሁሉም ያዉቅ ዘንድ ከሰማሁትና ካየሁት እንደሚከተለዉ አቅርቤላችኋለሁ፡፡ 

ፈቃደ እግዚአብሔር ቢሆን ወደፊት ታሪኩን የበለጠ በማስፋት በዐይን ምስክሮችና ዘመን በፈጠራቸዉ መሣሪያዎች ተቀነባብሮ ለሚቀጥለዉ የ50ኛ ዓመቱ በዓል የሚቀርብ መሆኑን በመጠቆም የታሪኩ ባለቤቶች እገዛችሁ እንዳይለየን እያሳሰብኩ ለዕለቱ እነሆ፦

በሰሜን አሜሪካ የኒዉዮርክ ቅድስት ሥላሴ ቤተ ክርስቲያን መንበረ ጵጵስና አመሠራረት ታሪክ  በአጭሩ
ግማሽ ምዕት ዓመት ለማስቆጠር በዋዜማ ላይ የሚገኝዉ መንበረ ጵጵስና እንዲመሠረት ምክንያት የሆነዉ ፋሺስት ኢጣልያ ኢትዮጵያን በወረረበት ወቅት እ.ኤ.አ በ1937 ገደማ ዶክተር መላኩ በያን በተባሉት ወርልድ ፌዴሬሽን የተባለ ድርጅት ተቋቁሞ እንደ ነበረና ከድርጅቱ ዓላማዎች አንዱ ለምዕራቡ ዓለም የሀገራችንን የኢትዮጵያንና የአፍሪካን ታሪክ ከማስተዋወቁም በላይ የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን በዕምራቡ ዓለም በአለንበት በሰሜን አሜሪካ እንዴት መቋቋምና መመሥረት እንዳለባት እቅድ
በማዉጣትና ወደ ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መንበረ ፓትርያርክ በመላላክ ግንኙነት እንዲፈጠር አስተዋጽኦ ማድረጉን ባለታሪኮች ያስረዳሉ፡፡

ከዚህም በመነሣት እ.ኤ.አ በ1952 አባ ገብረ ኢየሱስ መሽሻ በኋላ ብፁዕ አቡነ አትናቴዎስ ተብለዉ የምዕራቡ ዓለም ጳጳስ የነበሩትና አቶ አበራ ጀንበሬ በኋላ አባ አበራ ለቤተ ክርስቲያን አገልግሎት መስጫ የሚያስፈልጉትን ንዋያተ ቅዱሳት ይዘዉ ወደሰሜን አሜሪካ በመምጣት ቤተ ክርስቲያኑን በይፋ ለመክፈት ጥናቱን አጠናቀዉ ወደ ኢትዮጵያ ተመለሱ ይህ በእንዲህ እንዳለ በ1954 እ.ኤ.አ ብፁዕ አቡነ ቴዎፍሎስ የሐረር ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ባስልዮስ ረዳት በኋላም ብፁዕ ወቅዱስ አሜሪካንን በጎበኙበት ጊዜ በአሜሪካና በካሪቪያን ደሴቶች ለሚገኙት ለኢትዮጵያዉያንና ለምዕራቡ ዓለም ተወላጆች ቤተ ክርስቲያን ለማቋቋም ቅዱስ ሲኖዶስ ያሰበበት መሆኑን በማረጋገጥ በሥራ ለመተርጎም ራሳቸዉ ተመልሰዉ የሚመጡ መሆኑን በማስረዳትና ቃል በመግባት ተመለሱ። በገቡትም ቃል መሠረት እ.ኤ.አ ጥቅምት 25 ቀን 1959 ተመልሰዉ ወደ ሰሜን አሜሪካ በመምጣት ዛሬ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መንበረ ጵጵስና ሀገረ ስብከት ሆኖ አገልግሎት በመስጠት ላይ የሚገኘዉን የኒዉዮርክ ቅድስት ሥላሴ ቤተ ክርስቲያን ቅዳሴ ቤቱን አከበሩ፡፡ መርቀዉም ከፈቱ።

በሌላ መልኩ ባለ ታሪኮች እንደሚሉት የምዕራቡ ዓለም ተወላጆች የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን እምነት ተከታዮች ምእመናን በኒዉዮርክ ስቴት በብሩክሊን ከተማ ሕንፃ ቤተ ክርስቲያን ተገዝቶ በቅዱስ ሚካኤል ስም ተሰይሞ አገልግሎት በመስጠት ላይ እያለ ከአቅም ማነስ የተነሳ ታክስ ስላልተከፈለበት ማዘጋጃ ቤቱ እንደወረሰዉ ይተረካል።የኒዉዮርክ ቅድስት ሥላሴ ቤተ ክርስቲያን መንበረ ጵጵስና 140_142 ዌስት 176 ስትሪት ብሮንክስ 10453 ላይ የሚገኝ 

 ሲሆን ይህ ሕንፃ የአይሁድ ምኩራብ የነበረ ከምኩራብነትም ወደ ቤተ ክርስቲያን የተለወጠ መሆኑን እና በጊዜዉ ዋጋከአይሁዳዉያን በ55000 ዶላር እ.ኤ.አ ታሕሳስ 25 ቀን 1969 መገዛቱን መዛግብቱ ያስረዳሉ።በመቀጠልም ታሪኩ እንደሚገልጸዉ በባንክ ብድር በመገዛቱ የነበሩት ምእመናን የመክፈል አቅም አንሶአቸዉ ከላይ እንደተገለጸዉ እንደ ብሩክሊኑ ሕንፃ በዕዳ ሊወረስ ሲል  ፈቃደ እግዚአብሔር ሆኖ ግርማዊ ቀዳማዊ ዐፄ ኃይለ ሥላሴ እንደ አገራችን አቆጣጠር በጥቅምት ወር 1963 ዓ.ም የተባበሩት መንግሥታት በዓል ለማክበር ኒዉዮርክ በተገኙበት ወቅት በነበሩት የቤተ ክርስቲያን አባቶችና ምእመናን ችግሩ ተነግሯቸዉ ይህ ቤተ ክርስቲያን የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ንብረት በመሆኑና ለምዕራቡ ዓለም የሀገረ ስብከቱ መንበረ ጵጵስና ሆኖ በማዕከል አገልግሎት የሚሰጥ  መሆኑን አርቆ በማሰብ የነበረዉ ዕዳ 32000 ዶላር በመንበረ ፓትርያርኩ ዋስትና ከባንክ እንዲከፈል ትእዛዝ በመስጠታቸዉ ቤተ ክርስቲያኒቱ ከዕዳ ነጻ ሆና ከአለንበት ዘመን ደርሳለች፡፡  

በእርግጥ ባለፉት ዘመናት የኒዉዮርክ ቅድስት ሥላሴ ቤተ ክርስቲያን መንበረ ጵጵስና ዘርፈ ብዙ የሆኑ ችግሮች ተፈራርቀዉበታል፡፡ አልፎ ተርፎም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሀብትና ንብረት መሆኑ በልዩ ልዩ መዛግብት የተረጋገጠ ሲሆን ወቅትና ጊዜን በመጠቀም አሳልፎ ለመስጠት ብዙ ዉጣ ዉረዶች እንደተካሄዱ የትናንቱ ታሪክ ያስረዳናል። ሕንፃዉም የዕድሜ ባለጸጋ በመሆኑ የአልወድቅም ባይነት ይዞት እየተንገዳገደ ጠግኑኝ ድረሱልኝ የሚል አቤቱታ በየጊዜዉ ያቀርባል፡፡ ለአቤቱታዉ የሚሰጠዉ መልስ ግን አጥጋቢ አይደለም ከጥቂት አደራ ጠባቂዎች መለስተኛ ጥገና ከሚደረግለት በቀር መሠረታዊ ጥገና ለማድረግ የታሪክ ጠባቂዎች ዐቅም አልፈቀደም። ስለሆነም የአባቶቹን ታሪክ ለመጠበቅ ፈቃደኞች የሆኑትን ሁሉ ድረሱልኝ በማለት ጥሪዉን ያስተላልፋል።

ከዚህ በላይ የቀረበዉ የአባቶቻችን ታሪክ ሲሆን የአባቶቻችንን ታሪክ ለመጠበቅና ለመድገም እንደ ቤተ ክርስቲያናችን ሥርዓት ቤተ ክርስቲያኑ ዛሬ ከሚገኝበት ምድር ቤት ወጥቶ ራሱን በቻለ ቤተ መቅደስ ይከብር ዘንድ አባቶቻችን ባቆዩን ቦታ ለመሥራት ቅድመ ዝግጅቱ ተጠናቆ ማሠሪያዉ ገንዘብ የሚገኝበትን መንገድ በማፈላለግ ላይ እንገኛለን ስለሆነም ክርስቲያኖች ሁሉ የታሪኩ ባለቤቶች ይሆኑ ዘንድ ቤተ ክርስቲያን ጥሪዋን ታስተላልፋለች።

Home| Feedback| Webmaster
EOTC-DC Diocese., All Rights Reserved