:::ዜናዎች:::

:::ያግኙን :::

ርዕሰ አንቀጽ

ወጣቱ ወዴት ነው መሄድ ያለበት)
የቤተ ክርስቲያን ታሪክ በሃይማኖት ፍቅር በነደዱ፣ ለተጋድሎ ራሳቸውን በሰጡ የአባቶቻቸውን ታሪክ ለመድገም በቆረጡ ታሪክ ሠሪ ወጣቶች የተሞላ ነው፡፡ እነ አቤልን፣ እነ ይስሐቅን፣ እነ ያዕቆብን፣ ነቢዩ ዳንኤልን እና ሠለስቱ ደቂቅን፣ ባሮክን እና አቤሜሌክን በብሉይ ኪዳን እናገኛቸዋለን፡፡
ተጨማሪ

 

 
  ራእይ
 
የጥያቄዎ መልስ
  ሊቀ ጳጳሱን ይጠይቁ
  ስብከቶች

 
 
 

የቤተ ክርስቲያንን አንድነት መጠበቅ እና ማስጠበቅ መንፈሳዊ ግዴታችን ነው ።

Megelechaከቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ  ጉባኤ  ፍርድ እና ውሳኔ አንዲሰጠኝ ስለመጠየቅ: -ቀሲስ ዶክተር መስፍን ተገኝ

letter

በብፁዕ አቡነ ፋኑኡል የተጻፈ ደብዳቤን በመቃወም በኢ/ኦ/ተ/ቤተ ክርስቲያን በዋሸንግተን ዲሲና አካባቢው ሀገረ ስብከት ሥር በሚገኙ አብያተ ክርስቲያናት የተሰጠ የአቋም መግለጫ

ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የዋሽንግተን ዲሲና አካባቢው ሀገረ ስብከት ጽ/ቤት የተሰጠ መግለጫ

Megelecha


በዋሽንግተን ዲሲና አካባቢው ሀገረ ስብከት ሥር የሚገኙ አብያተ ክርስቲያናት አስቸኳይ ስብሰባ አደረጉ ”

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የዋሽንግተን ዲሲና አካባቢው ሀገረ ስብከት  መንፈሳዊ አስተዳደር ጉባኤ የጠራው አስቸኳይ ስብሰባ ጥር 25 እና 26 ቀን 2004 ዓ. ም በቻርለት  ሰሜን ካሮላይና  ተካሄዷል። ስብሰባው የተጠራው አብያተ ክርስቲያናቱ  ሀገረ ስብከቱ የሚደረገውን መንፈሳዊ እንቅስቃሴ ለመመልከት ዓመታዊ እቅድ አፈጻጸም ለመገምገምና  በቅዱስ ሲኖዶስ ፈቃደ የተመሰረተውን  ሀገረ ስብከት  መዋቅር ተቀብለው በኃላፊነት ላይ ካለው  የሀገረ ስብከቱ መንፈሳዊ አስተዳደር ጉባኤ ጋር ላለመስራት ብፁዕ አቡነ ፋኑኤል  ሊቀ ጳጳስ  በወሰዱት  የተናጠል አካሔድ የተፈጠረውን ችግር በመመርመር  መፍትሔ  እንዴት ሊገኝ እንደሚችል ለመመካከር እና የቤተ ክርስቲያን መዋቅር የበለጠ ተጠብቆ የሚሄድበትን መንገድ  ለመነጋገር ነው ።

በዚህ ስብሰባ ላይ ብፁዕ አቡነ ፋኑኤል  ሊቀ ጳጳስ  በቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ የተመሰረተውን ሀገረ ስብከትና በሕጋዊ መንገድ የተመረጠውን አስተዳደር መንፈሳዊ ጉባኤ በትክክል አምነውበት ቢገኙ ለብፁዕነታቸው ክብር ለቤተክርስቲያንም ሰላም ይሰጥ እንደነበረ የጉባኤው አባላት ገልጸዋል። ተጨማሪ

ብፁዕ አቡነ ፋኑኤል Abune Fanuel's VOA Interview & DC Archdiocese 1.21.12 from Misrake Teshaye K TekleHimanot .ብፁዕ አቡነ አብርሃም የአዲ">
ግንቦት ተክለሃይማኖት ፳፻፫ (Ginbot 2003 Nigis) from Misrake Teshaye K TekleHimanot

ad


Tinsae (2011) from Misrake Teshaye K TekleHimanot.

እንኳን ለብርሃነ ትንሣኤው በሰላምና 
    በጤና አደረሳችሁ

የዲሲ እና አካባቢው ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ አብርሃም  የጌታችንና የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስን የትንሣኤ በዓል ምክንያት በማድረግ ያስተላለፉት ቃለ ምዕዳን እና ቡራኬ፡፡

የሉዊቪል ኬንታኪ ደብረ ኃይል ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን ቅዳሴ ቤት ተከበረ።

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን በዋሺንግተን ዲሲና አካባቢው ሀገረ ስብከት የሉዊቪል ኬንታኪ ደብረ ኃይል ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን በሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ አብርሃም የተተከለው በሚያዝያ ወር 2001 ዓመተ ምህረት ሲሆን ከተተከለ ሁለት ዓመት ሳይሞላው ምንም እንኳን ቁጥራቸው ጥቂት ቢሆንም በሉዊቪል ከተማ በሚገኙ ምዕመናን እና በደብሩ አስተዳዳሪ በመልአከ ኃይል ፍቅረኢየሱስ ጋረደው ጥረት በሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ ያላሰለሰ ክትትል መመሪያ ሰጭነት ለቤተክርስቲያን ልጆች ሁሉ ኩራት የሆነ የቦታው ስፋት 4 ኤከር ለካቶሊክ ቤተክርሰቲያን በገዳምነት ያገለግል የነበረ ቦታ በ480,000 (በአራት መቶ ሰማንያ ሺ) ዶላር ተገዝቷል። ከዚህም ውስጥ 99,120 (ዘጠና ዘጠኝ ሺ አንድ መቶ ሃያ) ዶላር ለዳውን ፔይመንት ተከፍሏል። ቅዳሴ ቤቱም ብፁዕ አቡነ አብርሃም እና ብፁዕ አቡነ ማርቆስ በተገኙበት በቤተክርስቲያናችን ሥርዓት መሠረት በሊቃነ ጳጳሳቱ ተባርኮ ጥር 28 ቀን 2002 ዓ.ም ተከብሯል።

በልዩ ድምቀት በተከበረው በዓል ላይ የሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ አብርሃም እና ብፁዕ አቡነ ማርቆስ የተገኙ ሲሆን በሉዊቪል ኬንታኪ ከሚገኙ ምዕመናን በተጨማሪም በሀይማኖት ጽናት የወቅቱን የአየር ጠባይ በመቋቋም ከዲሲና አካባቢው ከቴነሲ፣ ከሜንፌስ ከአትላንታ፣ ከኢንድያናፖሊስ፣ ከሚዙሪ፣ ከኒውዮርክ፣ ከኒውጀርሲ እና ከሚሺጋን የመጡ የአድባራት አስተዳዳሪዎች፣ ካህነት ፣ ዲያቆናት እና ምዕመናን ተገኝተዋል።

የሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ አብርሃም በበዓሉ ላይ እንደተናገሩት … ‘’ብፁዕ ሕዝብ ዘእግዚአብሔር አምላኩ’’ እግዚአብሔር አምላኩ የሆነለት ሕዝብ ምስጉን ነው። የሚለውን በመጥቀስ የሉዊቪል ኬንታኪ ደብረ ኃይል ቅዱስ ገብርኤል አጥቢያ ምእመናን በምግባር በሃይማኖት ጎልብተው ፈቃደ ሥጋቸውን ለፈቃደ ነፍሳቸው አስገዝተው በአምልኮት ጸንተው በመንፈሳዊ ቅናት ተነሳስተው በሠሩት የሚያኮራ መልካም ሥራ አመስግነዋቸዋል።ለሚመለከታቸው የኮሚቲ አባላት ሽልማትና የምስክር ወረቀት ተሰጥቷቸዋል። ለሌላው የሰሜን አሜሪካ ምእመናን አርዓያ መሆናቸውንም በመግለጽ በሀገረ ስብከቱ ካሉ አብያተ ክርስቲያናት መካከል በቁጥር ብዛት አነስተኛ በአጭር ጊዜ ውስጥ የራስ ቤተ ክርስቲያን በመግዛት የመጀመሪያ በመሆናቸሁ መንፈሳዊ ኩራት ልትኮሩ ይገባችኋል በማለት አድንቀዋቸዋል፡፡ አያይዘውም ሀገረ ስብከቱ ይህን ቤተ ክርስቲያን ለወደፊቱ ደብር ወገዳም የማድረግ ዕቅድ እንዳለውና ምዕመኑ እንዳሁኑ ሁሉ በመጠንከር እስከመጨረሻው በአንድነት በመቆም ቀደሞ የነበረው ጸበል ተባርኮ ቦታው ተዘጋጅቶ ህዝበ ክርስቲያን የሚጠመቅበት ሱባዔ የሚይዝበት በሥራ የደከመ መንፈሱን አድሶ የሚመለስበት ደብር እና ገዳም ለማድረግ ጥረቱ እንዲቀጥል አሳስበዋል፡፡ምእመናኑም በልልታና በጭብጨባ ደስታቸውን ገልጸዋል። በማያያዝም ይህ አኩሪ ተግባር የኬንታኪ ምእመናንና የሀገረ ስብከቱ ብቻ ሳይሆን የመላው ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን መሆኑን የገለፁት ብፁዕ አቡነ ማርቆስ ምዕመኑ እንዲህ አይነቱን ተግባር አጥናክሮ እንዲቀጥል አባታዊ መልክታቸውን አስተላልፈዋል ሰፊ ትምህርት ሰጥተዋል።

የደብሩ አስተዳዳሪ መልአከ ኃይል ፍቅረኢየሱስ ጋረደው እንደገለጹት ለቤተክርስቲያኒቱ እዚህ ደረጃ መድረስ የሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ ብጹዕ አቡነ አብርሃም የቅርብ ክትትል በማድረግና ምዕመናንን በማበረታታት ግንባር ቀደም ሆነው በየብስም ባየርም በትደጋጋሚ በመመላለስ ታላቅ አስተዋጽዖ በማድረጋቸው ነው ብለዋል። የብፁዕነታቸውን አብነት በመከተልም የአጥቢያው ምዕመናን፣ የሰበካ ጉባኤውና የህንፃ ኮሚቴ አባላት ላደረጉት አገልግሎት ምስጋና አቅርበው የቅድስት ቤተክርስቲያን ልጆች ሁሉ እንኳን ደስ አለን በማለት “ያመኑትም ሕዝብ አንድ ልብ አንዲትም ነፍስ ነበራቸው” በሚል ርእስ የደስታና የምስጋና መልእክት አቅርበዋል።

Misrake Tsehaye K. TekleHimanot Sebaka Gubae Mircha from Misrake Teshaye K TekleHimanot

በሀገራችን ኢትዮጵያ የጥምቀት በዓል በታላቅ ክብር
እንዲከናወን መንፈሳዊ አገልግሎታቸውን ላበረከቱ የእግዚአብሔር ልጆ በሙሉ:-K. TekleHimanot Yelidet Be’al – Tahisas 2003 from Misrake Teshaye K TekleHimanot

የዲሲ እና አካባቢው ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ
አቡነ አብርሃም አዲስ ዓመትን ምክንያት በማድረግ ቃለ ምዕዳን እና ቡራኬ አስተላለፉ፡፡

ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ስለ ሰላምና አንድነት ከተላከው ልዑክ የተሰጠ መግለጫ

qaleawadie


እንኳን ለብርሃነ ትንሣኤው በሰላምና 
    በጤና አደረሳችሁ

የዲሲ እና አካባቢው ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ አብርሃም  የጌታችንና የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስን የትንሣኤ በዓል ምክንያት በማድረግ ያስተላለፉት ቃለ ምዕዳን እና ቡራኬ፡፡

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ  ፩ዱ አምላክ አሜን
  
meleket

 

የዲሲና አካባቢው ሀ/ስብከት ያዘጋጀው ከመጋቢት 17-19(March 26 - 28) ጉባዔ ተካሄደ

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን የዋሽንግተን ዲሲና አካባቢው ሀገረ ስብከት የምሥራቀ ፀሐይ አቡነ ተክላ ሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን(መንበረ ጵጵስና) ከመጋቢት 17-19(March 26 - 28) “መንጋውም አንድ እረኛውም አንድ”ዮሐ10፣16፡፡ በሚል መሪ ቃል የሦስት ቀናት ትምህርታዊ ጉባኤ አካሂዷዋል ፡፡

ይህ ታላቅ መንፈሳዊ መርሃ ግብር  በብፁዕ አቡነ አብርሃም የዋሽንግተን ዲሲና አካባቢው ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በጸሎት የተከፈተ ሲሆን መምህራነ ወንጌል  ሰሞነ ህማማትንና ወቅቱን መሰረት ያደረጉ መልእክቶችን አስተላልፈዋል በተለይ የሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ አብርሃም ቀኖና ቤተ ክርስቲያንን በተመለከተ ሰፊ ትምህርት አስተላልፈዋል፣ እንዲሁም ከጉባኤው ተሳታፊዎች ለቀረበላቸው የተለያዩ ጥያቄዎች መልስ የሰጡበት መርሃ ግብር የብዙዎችን ስሜት የገዛ ሲሆን ከስዓት እጥረት የተነሳ የብዙዎችን ጥያቄ ለማስተናገድ ባለመቻሉ የምእመኑን የተለያዩ ጥያቄዎች ለማስተናገድ በቅርቡ ሀገረ ስብከቱ ጉባኤ እንደሚዘረጋ ለጉባኤው ታዳሚዎች ቃል ገብተዋል

የዝግጅቱ ከፊል ገፅታ እነሆ፡-     

ሻርለት የአንቀጸ ምሕረት በዓታ ለማርያም ቤተ ክርስቲያን ቅዳሴ ቤት በደማቅ ሁኔታ ተከበረ

በያዘነው ወር በአገራችን አቆጣጠር  የካቲት ፮ ቀን ፳፻፪ ዓ.ም  በኖርዝ ካሮላይና  ሻርለት የአንቀጸ ምሕረት በዓታ ለማርያም ቤተ ክርስቲያን ቅዳሴ ቤት በደማቅ ሁኔታ ተከበረ።

በቅዳሴ ቤቱ በዓል ብፁዕ አቡነ አብርሃም የዲሲና አካባቢው ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ተገኝተው በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሕግና ሥርዓት መሠረት
ባርከው የከፈቱ ሲሆን በበዓሉ ለተገኙት ምእመናን እና ምእመናት ጥንታዊትና ሐዋርያዊት የሆነችዉን ቤተ ክርስቲያን እምነትና ሥርዓት በመጠበቅና በማስጠበቅ ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ  አስተምረዋል።

የቤተ ክርስቲያኒቱም መመሥረት  ምእመናን እና ምእመናት ከአምላካቸው ጋር የሚገናኙባትና የሚያመልኩባት ቅዱስ ወንጌልን የሚማሩባት ሰላምና እና ዕርቅን ገንዘብ በማድረግ ሥዓርተ ቤተ ክርስቲያንን አውቀው በቅንነትና በታዛዥነት የሚመላለሱባት እንጂ ሰዎች በተለምዶ እነገሌ ቤተ ክርስቲያን ስለከፈቱ እኛም መክፈት አለብን በሚል የንግድ ሥርዓት የተከፈተ አለመሆኑን አስገንዝበዋል።
ከዚህም ጋር ለቤተ ክርስቲያኒቱ ምሥረታ በጉልበታቸውና በገንዘባቸው ክርስቲያናዊ ግዴታቸውን የተወጡትን በቤተ ክርስቲያኒቱ ስም አመስግነው ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያንን በመጠበቅ የሚያስተዳድሩና የሚመሩ ካህን ለቦታው በመመደብ  ጸሎተ ምሕላ ተደርጎ ቃለ ምዕዳን ከሰጡ በኋላ የበዓሉ ፍጻሜ ሆኖአል።

በአትላንታ የመካነ ሕይወት አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ
ቅዳሴ ቤት ተባርኮ አገልግሎት መስጠት ጀመረ፡፡

በአትላንታ የመካነ ሕይወት አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ
ቤተክርስቲያን ጥር 05 ቀን ፳፻2 (January 23 2010) በብጹዕ አቡነ አብርሃም በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የዋሽንግተን እና አካባቢው ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ እና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል ቅዳሴ ቤቱ ተባርኮ አገልግሎት መስጠት ጀመረ፡፡
በእለቱም ብጹዕ አቡነ ማርቆስ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስተዋህዶ ቤተክርስቲያን የስብከተ ወንጌል የበላይ ሀላፊ እና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል በእንግድነትተገኝተዋል፡፡ እንዲሁም በአካባቢው በሚገኙ አብያተ ክርስቲያናት የሚያገለግሉ ሊቃውንተ ቤተክርስቲያን ከሌሊቱ 4፡00 am ጀምሮ ተገኝተው በአሉን በተመለከተ ስብሐተ እግዚአብሔርአድርሰዋል፡፡
ተጨማሪ

የጻድቁ አባታችን የቅዱስ ተክለሃይማኖት በዓለ ልደት በታላቅ ድምቀት ተከበረ።


የዲሲ እና አካባቢው ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ አብርሃም አዲስ ዓመትን ምክንያት በማድረግ ቃለ ምዕዳን እና ቡራኬ አስተላለፉ፡፡

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አምላክ አሜን፡፡

በአለንበት አገር በሰሜን አሜሪካ፤ በሀገራችን በኢትዮጵያና በልዩ ልዩ አኅጉራት የምትገኙ አባቶቼና እናቶቼ ወንድሞቼና እኅቶቼ …. ተጨማሪየጻድቁ አባታችን የቅዱስ ተክለሃይማኖት በዓለ እረፍት በታላቅ ድምቀት ተከበረ።

እሑድ ነሐሴ 24 ኢትዮጵያዊው ጻድቅ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ሩጫቸውን በድል አድራጊነት ያጠናቀቁበት ገድላቸውን የፈጸሙበትና ከዚህ ዓለም ወደ ማያልፈው ዓለም የተሸጋገሩበት ቀን በመሆኑ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን በደመቀ ሁኔታ ይከበራል።ዘንድሮ ዲሲና አካባቢው ሀዲስ ሐዋርያ የተባሉት ኢትዮጵያዊውን

ጻድቅ በስማቸው በተሰየመው ቤተ ክርስቲያን ተገኝቶ ለማክበርና የበረከታቸው ተሳታፊ ለመሆን እድል ገጥሞታል።
 በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን የዲሲና አካባቢው ሀገረ ስብከት መንበረ ጵጵስና የምስራቀ ፀሓይ ቅዱስ ተክለ ሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን ለመጀመሪያ ጊዜ የቅዱስ አባታችንን በዓለ ንግስ በደመቀ ሁኔታ አክብርዋል።

በበዓሉ ላይ የዲሲና አካባቢው ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብጹዕ አቡነ አብርሃም ከተለያዩ የሰሜን አሜሪካ ግዛቶች የመጡ ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን ፣ቀሳውስት፣ ዲያቆናት፣ የሰንበት ትምህርት ቤቶች አባላትና የቤተ ክርስቲያን ፈርጥ የሆኑ ምእመናን ምእመናት ተገኝተዋል።

ከማለዳው አስር ሰዓት የጀመረው ስብሃተ እግዚአብሄር ደማቅና መንፈስ እግዚአብሄር የረበበት ነበር ቢባል ማጋነን አይሆንም።  በብጹ አቡነ አብርሃም የተመራው ቅዳሴ ከተፈጸመ በኋላ ብጹዕነታቸው ትምህርትና ቃለ ምዕዳን አስተላለፈው ታቦቱ ወደ መንበረ ክብሩ ተመልሱዋል፤  ከቀኑ ሰባት ሰዓት ላይ ሰርኦተ ህዝብ ሆኑዋል። 


ሐምሌ ፲፬ ቀን ፳፻ወ፩ ዓ.ም
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ ፩ አምላክ አሜን
“የቀረውንም ነገር ሳልቆጥር ዕለት ዕለት የሚከብድብኝ የአብያተ ክርስቲያናት ሁሉ ሀሳብ ነው።”   ፪ቆሮ፲፩፡ ፳፱

የወቅቱን የቤተ ክርስቲያን ችግር በማስመልከት ብፁዕ አቡነ አብርሃም የዋሽንግተን ዲሲና አካባቢው ሀገረ ስብከት ሊቀጳጳስ ያስተላለፉት መልእክትpdf

የዲሲና አካባቢው ሀ/ስብከት ያዘጋጀው ጉባዔ ተካሄደ

(ቨርጂኒያ)፦ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የዲሲና አካባቢው ሀ/ስብከት ያዘጋጀው ሦስት ቀናት የትምህርት፣ የጸሎትና የገቢ ማሰባሰቢያ ዝግጅት በተሳካ ሁኔታ ተካሄደ። ከአርብ ሰኔ 26-28/2001 ዓ.ም (ከጁላይ 3-5/2009) ድረስ የሀ/ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ አብርሃም በተገኙበት የተካሄደው ይህ ጉባዔ የቤተ ክርስቲያንን አንድነትና ልዕልና የክርስቲያኖችን ኃላፊነት

በሚያሳዩ የተለያዩ ርዕሶች ዙሪያ ትምህርቶች የተሰጡበት ሲሆን በተለያዩ መዘምራንም ጣዕመ ዝማሬዎች ተዘምረዋል።

“ሱታፌ ምእመናን በቤተ ክርስቲያን”፣ “ዕለት ዕለት የሚከብድብኝ የአብያተ ክርስቲያናት ሁሉ አሳብ ነው”፣ “አንተ ከፊቴ እንደቆምህ አላወቅሁም ነበር”፣ የእግራችሁጫማየሚረግጠውንቦታሁሉለእናንተሰጥቼአለሁ“ነአምን በአሐቲ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን፤ በአንዲት ቅድስት ቤተ ክርስቲያን እናምናለን”  በሚሉ ርእሶች ሰፊ ትምህርቶች በተለያዩ መምህራን የተሰጡ ሲሆን “የቤተ ክርስቲያን አስተዳደራዊ መዋቅር” በሚል ርእስ በስላይድ የተቀናበረ ዝግጅትም ቀርቧል።
በየዕለቱ ከጉባዔዎቹ ፍጻሜ በፊት ቃለ ምዕዳናቸውን፣ ትምህርታቸውንና ምክራቸውን የሰጡት ብፁዕነታቸው የትምህርቶቹን ማጠቃለያ ከመስጠታቸውም በላይ የየዕለቱን ወንጌሎችና ምስባካት በማብራራት አስተምረዋል። ሀገረ ስብከቱን ለማጠናከር መዋጮና የቃል መግባት ሥነ ሥርዓት የተከናወነ ሲሆን ጉባዔው ወደፊት እንዲቀጥል ከምዕመናን የቀረበው ጥያቄ ተቀባይነት አግኝቷል።
በዚሁ ታላቅ የጸሎትና የስብከተ ወንጌል ጉባዔ ላይ ቃለ ምዕዳናን የሰጡት ብፁዕ አቡነ አብርሃም በዲሲና በአካባቢው የሚገኙ አበው ካህናትና ምእመናን በሙሉ በአንድነት  ስለ አንዲቱ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን እንዲያገለግሉ ጥሪ አስተላልፈዋል። ዘመኑ የምንለያይበት አይደለም ያሉት ብፁዕነታቸው አባቶቻችን በደማቸው ፍሳሽ፣ በአጥንታቸው ክስካሽ ለዚህ ትውልድ ስላደረሷትና ወልድ ዋሕድ ብለን ስለምናምናት እምነት ሁላችንም የበኩላችንን ድርሻ ልንወጣ ይገባል ብለዋል።
በዚህ የሦስት ቀናት መርሐ ግብር ላይ ለመሳተፍ ከዲሲ፣ ከሜሪላንድና ቨርጂኒያ ቅርብ አካባቢዎች ከመጡት ምእመናን በተጫማሪ በብዙ ማይሎች ከሚገኙት ከኒውዮርክ ቡፋሎ፣ ከፔንሲልቬኒያ፣ ከባልቲሞርና ከሌሎችም ቦታዎች ምእመናን መገኘታቸው ብዙዎችን አስገርሟል። የዲሲና አካባቢው ሀ/ስብከት በቅርቡ የመንበረ ጵጵስና ሕንጻ ባለቤት የሆነ ሲሆን የጻድቁ አባታችን የቅዱስ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን ቅዳሴ ቤትም በበዓለ ጰራቅሊጦስ ዕለት ተከብሮ አገልግሎት መስጠት መጀመሩን መዘገባችን ይታወሳል።     

 

በዲሲና አካባቢው ሀገረ ስብከት የምሥራቀ ፀሐይ ቅ/ተክለሃይማኖት
ቤተ ክርስቲያን /መንበረ ጵጵስና/ቅዳሴ ቤት በደማቅ ሁኔታ ተከበረ

ክፍል 2        ክፍል 3
ክፍል 4        ክፍል5

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በዲሲና አካባቢው ሀገረ ስብከት የምሥራቀ ፀሐይ ቅ/ተክለሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን /መንበረ ጵጵስና/ ቅዳሴ ቤት ግንቦት 30 ቀን 2001 ዓ.ም /ጁን 7 2009/ በሀገረ ስብከቱ ሊቀጳጳስ በብፁዕ አቡነ አብርሃም፤

በመሥራች ኮሚቴው እና አባላቱ ከፍተኛ ጥረት በፈቃደ እግዚአብሔር “የቤተ ክርስቲያን የልደት ቀን” በሆነው በበዓለ ጰራቅሊጦስ ቀን በቨርጂንያ (115 ዋሽንግተን ስትሪት አሌክሳንደሪያ ቨርጂንያ) ተከበረ።

በቅዳሴ ቤቱ አከባበር ላይ ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን የሰንበት ት/ቤት መዘምራን፣ ቁጥራቸው የበዛ ምእመናን እና ምእመናት ተገኝተው መንፈሳዊ ደስታቸውን በዕልልታና በጭብጨባ አስተጋብተዋል።

ብፁዕነታቸው በክብረ በዓሉ ለተገኙት ምእመናን በአስተላለፉት ቃለ ምእዳን እና ቡራኬ “በሀገረ ስብከቱ የተመሠረተው የመንበረ ጵጵስናው ቤተ ክርስቲያን፤ ሥርዓትን ጠብቆ የተመሠረተ“ መሆኑን ገልጸዋል። ከዚህም ባሻገር “የቤተ ክርስቲያንን ዶግማ፤ ቀኖናና ትውፊት ሳይከለስና ሳይበረዝ ለነገው ተተኪ ትውልድ ለማስተላለፍ እና ለማስረከብ መንፈሳዊ ግዴታ” ያለብን መሆኑን በአጽንዖት ገልጸው “መለያየትን እና መመከፋፈልን ለማስወገድ ይልቁንም የተለያየን አንድ ሆነን የተጣላን ታርቀን የቤተ ክርስትያናችንን ህልውና ጠብቀን ለትውልዱ ማቆየት አማራጭ የሌለው መፍትሄ ከመሆኑም በላይ በመለያየትና በመከፋፈል አንድነትን ማምጣት የማይቻል” መሆኑን አስረድተዋል።

ብፁዕነታቸው ከዚህ በማያያዝ “በመቀራረብና በመመካከር ለችግሮች መፍትሄ በመፈለግ የእናታችን የቅድስት ቤተ ክርስቲያን ህልውና እንዲጠበቅ፤ ቤተ ክርስቲያናችን የወላድ መካን በመሆን ሀዘንተኛ እንዳትሆን፤ ውድቀቷን ለሚፈልጉ ተቃዋሚዎቿ እንዳትጋለጥ፤ ጉዳዩን በቸልተኛነት ማየት የለብንም” ብለዋል።

በመጨረሻም  “የታሪክ ተወቃሾች እንዳንሆን ልጆችሽ አለን በማለት የሕጓ ጠባቂዎች፣ የሥርዓቷ ፈጻሚዎች እንድንሆን ቤተ ክርስቲያን የእናትነት ጥሪዋን ታስተላልፋለች” ሲሉ ብፁዕነታቸው ለሁሉም ጥሪያቸውን አቅርበዋል። በሌላ መልኩም ሀገረ ስብከቱ በማኅበራዊና መንፈሳዊ ጉዳዮች ላይ ሕገ ቤተ ክርስቲያንን በመጠበቅ ካህናትን እና ምእመናንን በማስተባበር የሚሠራ እና የሚያሠራ መሆኑን አስገንዝበዋል።

በዚህ መልክ ከሌሊት የተጀመረው አገልግሎት ታቦተ ሕጉ ዑደት አድርጎ ከገባ በሁዋላ በብፁዕነታቸው ጸሎትና ቡራኬ ተጠናቋል።


የዲሲና አካባቢው ሀገረ ስብከት መንበረ  ጵጵስና ግዢ ተከናወነ

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የዲሲና አካባቢው ሀገረ ስብከት ከአንድ ዓመት በላይ በትጋትሲሠራበት የነበረውን የመንበረ ጵጵስና ግዢ በእግዚአብሔር ቸርነት፣ በድንግል ማርያም አማላጅነት በአባቶችና በምእመናን ትጋትና ርብርብ ተግባራዊ ሊያደርግ

Hagere Sebeket

መቻሉን የሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ አብርሃም አበሰሩ። በትንሣዔ ማግስት፣ በቅ/ሚካኤል ወርሃዊ በዓል መታሰቢያ ዕለት እና በማዕዶት ቀን ይህ ታላቅ ዜና መሰማቱ በአገልግሎቱ የተሳተፉትን በሙሉ ከልብ አስደስቷል።

በቃለ ዐዋዲ ዐንቀጽ አርባ ሦስት ቁጥር አንድ ላይ እንደ ተገለጠው «የመንበረ ጵጵስና ሀገረ ስብከት ጽ/ቤት በሀገረ ስብከቱ ክልል ውስጥ ለሚገኙ ገዳማት፣ አድባራት እና የገጠር አብያተ ክርስቲያናት እንዲሁም በየደረጃው ለተቋቋሙት ሰበካ መንፈሳውያን ጉባኤያትና ለወረዳ ቤተ ክህነት የሥራ አመራርና ከፍተኛ የአስተዳደር ኃላፊነት ያለው” እና  በአንድ የተወሰነ ክልል ቤተ ክህነቱን ወክሎ የሚሠራ ተቋም ሲሆን፣ ሃይማኖቱን እና ቀኖናውን ለመጠበቅ እና ለማስጠበቅ፣ ከሐዋርያት  ጀምሮ የመጣውን ሀብተ ክህነት ለመጠበቅ እና ለማስተላለፍ፣ ስብከተ ወንጌል እንዲስፋፋ፣ ገዳማት እና አድባራት እንዲረዱ፣ አብያተ ክርስቲያናት እንዲተከሉ፣ ምእመናን ተገቢውን አገልግሎት እንዲያገኙ፣ የቤተ ክርስቲያኒቱ ሕጋዊ መብት እንዲከበር፣ የቤተ ክርስቲያኒቱ አገልግሎት ወጥ እና ሥርዓቱን የጠበቀ እንዲሆን፣ የካህናት አስተዳደር እና አገልግሎት በቤተ ክርስቲያኒቱ ሕግ መሠረት እንዲሆን፣ የቤተ ክርስቲያኒቱ ሀብት እና ንብረት በሕግ እና በሥርዓት መሠረት እንዲጠበቅ፣ ምእመናን በቤተ ክርስቲያኒቱ ተገቢውን አገልግሎት እንዲያገኙ እና እንዲሰጡ ያደርጋል።

ተጨማሪ

እንኳን ለብርሃነ ትንሣኤው በሰላምና 
    በጤና አደረሳችሁ

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ  ፩ዱ አምላክ አሜን
  
 
 
 
በቀሲስ ነህምያ ጌቱ

ታህሳስ ፳፱ ቀን ፳፻፩ ዓ.ም

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ ፩ አምላክ አሜን  

ብፁዕ አቡነ አብርሃም የልደት በዓልን ምክንያት በማድረግ ያስተላለፉት ቃለ ምዕዳን እና ቡራኬ
በአለንበት አገር በሰሜን አሜሪካ፤ በሀገራችን በኢትዮጵያና በልዩ ልዩ አኅጉራት የምትገኙ አባቶቼና እናቶቼ ወንድሞቼና እኅቶቼ ከሁሉ አስቀድሞ ለጥበቃዉና ለመግቦቱ ወሰን የሌለበት ልዑል እግዚአብሔር በረድኤት ጠብቆ ሰላም እርቅ ለተመሠረተበት ሰውና መላእክት በአንድነት ለዘመሩበት እንኳን ለብርሃነ ልደቱ በሰላም አደረሳችሁ በማለት በሀገረ ስብከቱ ስም መልካም ምኞቴን አቀርባለሁ።  

ተጨማሪ

 
 

  የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት ምን ለምን እንዴት 

የሰንበት ት/ቤቶች አንድነትና የአንድነት ፍሬ በተለያዩ አጋጣሚዎች ታይቷል፡፡ይሁን እንጂ አንድነቱ የተጠናከረ ባለመሆኑ የተከሰቱ ችግሮችም አሉ፡፡ ለአንድነቱ መላላት ምክንያት የሆኑቱን በሁለት ከፍሎ መመልከት መልካም ነው ፡፡እነርሱም ዉጫዊና ዉስጣዊ ችግሮች ናችዉ፡፡

ተጨማሪ

 
መኑ አንተ? አንተ ማነህ?  

የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን በሃይማኖት ለወለደቻቸዉ  ልጆቿ ብቻ ሳትወሰን  ለኢትዮጵያዉያን ወገኖቿ ሁሉ የመጀመሪያዉን ትምህርት ቤት በመክፈት ሥነ ጽሑፍን[፣ ሥነ ጥበብን፣ ሥነ ስዕልን፣ አስተዳደርን፣ በብቃትና  በትጋት አስተምራለች። ከዚህም ጋር በጋራ የአገር ድንበር መጠበቅን፣ በሀዘን በደስታ ተባብሮና ተደጋግፎ መኖርን፣ ለትዉልድ ሁሉ አበርክታለች።  አበዉ እንደሚሉት ታሪክ ትልቅ ትምህርት ቤት ከመሆኑም በላይ መስተዋት ነዉና ከመልካም ታሪኳ እንደተማርነዉና እንደተረዳነዉ እዉነተኛ ልጆቿን ለይታ የምታዉቅ በመሆኗ መልካም ስምን ሰጥታ ሞግስን እና ክብርን አጎናጽፋ ትልቅ ትንሽ፣ ነጭ ጥቁር፣ ሩቅ ቅርብ፣ ዘመድ ባዕድ ሳትለይ እናትነቷን አዉቀዉ፣ ጥሪዋን ሰምተዉ፣ ሥራቷን ተቀብለዉ፣ ሕጓን አክብረዉ ለሚመላለሱት ሁሉ አድልዎ በሌለበት የእናትነት ፍቅሯ የማይጠፋ የዘለዓለም ስምና ክብር ከድል አክሊል ጋር አቀዳጅታለች። 

 if you can't read this website click here and install the font. 

የዲሲ እና አካባቢው ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳሳት


ብፁዕ አቡነ አብርሃም


ብፁዕ አቡነ ቀውስጦስ

ብፁዕ አቡነ አብርሃም ያስተላለፉት ቃለ ምዕዳን እና ቡራኬ

ብፁዕ አቡነ አብርሃም የአዲ ዓመት በዓልን ምክንያት በማድረግ ያስተላለፉት ቃለ ምዕዳን እና ቡራኬ

ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተላለፈ ቃለ ውግዘት 

English Version Letter , Resolution

 
Home| Feedback| Webmaster
EOTC-DC Diocese., All Rights Reserved