:::ዜናዎች:::

:::ያግኙን :::

ርዕሰ አንቀጽ

ወጣቱ ወዴት ነው መሄድ ያለበት)
የቤተ ክርስቲያን ታሪክ በሃይማኖት ፍቅር በነደዱ፣ ለተጋድሎ ራሳቸውን በሰጡ የአባቶቻቸውን ታሪክ ለመድገም በቆረጡ ታሪክ ሠሪ ወጣቶች የተሞላ ነው፡፡ እነ አቤልን፣ እነ ይስሐቅን፣ እነ ያዕቆብን፣ ነቢዩ ዳንኤልን እና ሠለስቱ ደቂቅን፣ ባሮክን እና አቤሜሌክን በብሉይ ኪዳን እናገኛቸዋለን፡፡
ተጨማሪ

 
 
  ራእይ
 
የጥያቄዎ መልስ
  ሊቀ ጳጳሱን ይጠይቁ
 
 

የዲሲና አካባቢው ሀገረ ስብከት መንበረ  ጵጵስና ግዢ ተከናወነ

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የዲሲና አካባቢው ሀገረ ስብከት ከአንድ ዓመት በላይ በትጋት ሲሠራበት የነበረውን የመንበረ ጵጵስና ግዢ በእግዚአብሔር ቸርነት፣ በድንግል ማርያም አማላጅነት በአባቶችና በምእመናን ትጋትና ርብርብ ተግባራዊ ሊያደርግ መቻሉን የሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ አብርሃም አበሰሩ። በትንሣዔ ማግስት፣ በቅ/ሚካኤል ወርሃዊ በዓል መታሰቢያ ዕለት እና በማዕዶት ቀን ይህ ታላቅ ዜና መሰማቱ በአገልግሎቱ የተሳተፉትን በሙሉ ከልብ አስደስቷል።
በቃለ ዐዋዲ ዐንቀጽ አርባ ሦስት ቁጥር አንድ ላይ እንደ ተገለጠው «የመንበረ ጵጵስና ሀገረ ስብከት ጽ/ቤት በሀገረ ስብከቱ ክልል ውስጥ ለሚገኙ ገዳማት፣ አድባራት እና የገጠር አብያተ ክርስቲያናት እንዲሁም በየደረጃው ለተቋቋሙት ሰበካ መንፈሳውያን ጉባኤያትና ለወረዳ ቤተ ክህነት የሥራ አመራርና ከፍተኛ የአስተዳደር ኃላፊነት ያለው” እና  በአንድ የተወሰነ ክልል ቤተ ክህነቱን ወክሎ የሚሠራ ተቋም ሲሆን፣ ሃይማኖቱን እና ቀኖናውን ለመጠበቅ እና ለማስጠበቅ፣ ከሐዋርያት  ጀምሮ የመጣውን ሀብተ ክህነት ለመጠበቅ እና ለማስተላለፍ፣ ስብከተ ወንጌል እንዲስፋፋ፣ ገዳማት እና አድባራት እንዲረዱ፣ አብያተ ክርስቲያናት እንዲተከሉ፣ ምእመናን ተገቢውን አገልግሎት እንዲያገኙ፣ የቤተ ክርስቲያኒቱ ሕጋዊ መብት እንዲከበር፣ የቤተ ክርስቲያኒቱ አገልግሎት ወጥ እና ሥርዓቱን የጠበቀ እንዲሆን፣ የካህናት አስተዳደር እና አገልግሎት በቤተ ክርስቲያኒቱ ሕግ መሠረት እንዲሆን፣ የቤተ ክርስቲያኒቱ ሀብት እና ንብረት በሕግ እና በሥርዓት መሠረት እንዲጠበቅ፣ ምእመናን በቤተ ክርስቲያኒቱ ተገቢውን አገልግሎት እንዲያገኙ እና እንዲሰጡ ያደርጋል

ሀገረ ስብከት ለመጀመርያ ጊዜ በሥራ ላይ የዋለው ቅዱሳን ሐዋርያት የጌታችንን ትምህርት ተግባራዊ ለማድረግ ዓለምን ዕጣ በዕጣ ተከፋፍለው ለማስተማር በወጡ ጊዜ ነው፡፡ ቅዱሳን ሐዋርያት ይመቻል፣ አይመችም ሳይሉ በተሠማሩበት ሀገረ ስብከት ገብተው አብያተ ክርስቲያናትን በመትከል፣ ምእመናንን አስተምረው በማጥመቅ፣ ካህናትን እና ዲያቆናትን በመሾም የወንጌልን ቃል ለዓለም አዳርሰዋል፡፡ ቅዱስ ጴጥሮስ በሮም ሀገረ ስብከቱ፣ ዮሐንስ ወንጌላዊው በታናሽ እስያ ሀገረ ስብከቱ፣ ቶማስ በሕንድ ሀገረ ስብከቱ፣ማርቆስም በእስክንድርያ የሠሩት ሥራ ለዚህ ማስረጃችን ነው፡፡ 

office

በግብጽ ቤተ ክርስቲያን ታሪክ መጀመርያ የነበረው የእስክንድርያ መንበር ብቻ ሲሆን በኋላ ግን እስክንድርያ የፓትርያርኩ መንበር ሆና በየአካባቢው አህጉረ ስብከት ተመሠረቱ፡፡ በኢትዮጵያውያን ነገሥታት እና ሕዝብ በጎ ፈቃድ እና አርቆ አስተዋይነት ወደ እስክንድርያ ተልኮ ለጵጵስና የበቃው የመጀመርያው ጳጳስ ፍሬምናጦስ ሀገረ ስብከት «ጳጳስ ዘአኩስም ወዘኩላ ኢትዮጵያ» ተብሎ ከተመለሰበት ጊዜ ጀምሮ የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን በእስክንድርያ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ሥር እንደ አንድ ሀገረ ስብከት ሆና ከአንድ ሺህ አምስት መቶ ዘመናት በላይ መቆየቷ ይታወቃል።  
የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን የራስዋን አህጉረ ስብከት መመሥረት የጀመረችው ከራስዋ ልጆች መካከል ፓትርያርክ ባገኘች ጊዜ ሲሆን በ1943 ዓም የመጀመርያው ኢትዮጵያዊ ፓትርያርክ ሆነው የተሾሙት ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ባስልዮስ አቡነ ታዴዎስን ለጎሬ፣ አቡነ ገብርኤልን ለወሎ፣ አቡነ ማርቆስን ለኤርትራ፣ አቡነ ፊልጶስን ለኢየሩሳሌም፣ አቡነ ጎርጎርዮስን ለከፋ ጳጳሳት አድርገው ሾመው እንደነበር የታሪክ ድርሳናት ያወሳሉ፡፡ ቆይቶም በ1948 ዓ.ም ትግራይ በሀገረ ስብከትነት ተቋቁሞ ብፁዕ አቡነ ዮሐንስ ተሾመውበታል፡፡ 
በኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን የአህጉረ ስብከት ቁጥር በየጊዜው እያደገ መጥቶ፣ ብጹዕ አቡነ ጎርጎርዮስ «የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ታሪክ» በተሰኘው መጽሐፋቸው እንደገለጡት፣ በ1974 ዓ.ም የአህጉረ ስብከቱ ዕድገት ወደ አሥራ ዘጠኝ ያህል ደርሶ ነበር፡፡ በአሁኑ ጊዜ ደግሞ «የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ታሪክ ከልደተ ክርስቶስ እስከ 2000 ዓ.ም» የተሰኘው  የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት መጽሐፍ እንደሚገልጠው አርባ በሀገር ውስጥ፣ ስምንት ከሀገር ውጭ፤ በድምሩ አርባ ስምንት አህጉረ ስብከት ይገኛሉ፡፡ 
የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ከሀገር ውጭ የመጀመርያውን ሀገረ ስብከት ያቋቋማቸው ነሐሴ 28 ቀን 1943 ዓ.ም ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ባስልዮስ አቡነ ፊልጶስን የኢየሩሳሌም ሊቀ ጳጳስ አድርገው በሾሟቸው ጊዜ ሲሆን በምዕራቡ ዓለም የነበረው የቤተ ክርስቲያን እንቅስቃሴ በ1945 ዓ.ም ሲጀመር የምዕራቡ ዓለም «ምዕራባዊው ንፍቀ ክበብ፣ Western Hemisphere» በሚል አንድ ሀገረ ስብከት ተደርጎ ተቋቋመ። በኋላም እ.ኤ.አ በ1992 ቅዱስ ሲኖዶስ ባደረገው ጉባኤ ይህንን ሀገረ ስብከት አራት አህጉረ ስብከት (ማለትም ዩናይትድ ስቴትስ ኦፍ አሜሪካ እና ካናዳ፣ የካሪቢያን ደሴቶች እና ደቡብ አሜሪካ፣ ምዕራብ አውሮፓ እና ምሥራቅ አፍሪካ) እንዲሆን በማድረግ ሊቃነ ጳጳሳት ተሾሙባቸው፡፡ 


እኤአ በ1995 የዩናትድ ስቴትስ እና የካናዳ አህጉረ ስብከት ወደ ሁለት ተከፍለው ካናዳ ለብቻው ዩናይትድ ስቴትስም ለብቻው ተቋቋመ፡፡ በ1998 ዓ.ም ደግሞ ዩናይትድ ስቴትስ ወደ ሦስት ተከፋፍሎ የካሊፎርኒያ እና አካባቢው፣ ዋሽንግተን ዲሲ እና አካባቢ እንዲሁም የሰሜን ምሥራቅ፣ የደቡብ ምሥራቅ እና የመካከለኛው አሜሪካ የኒውዮርክ ሀገረ ስብከት ተብሎ ሦስት ሊቃነ ጳጳሳት ተሾሙበት፡፡  በ1985 ዓ.ም የአፍሪካ፣ በ1997 ዓ.ም የዓረብ ኤምሬትስ እና የአካባቢው ሀገረ ስብከት፣ በ1998 ዓ.ም የአውስትራልያ ሀገረ ስብከት፣ በ1998 ዓ.ም የደቡብ አፍሪካ አሀጉረ ስብከት ከኢትዮጵያ ውጭ ሲቋቋሙ  ቤተ ክርስቲያናችን ከሀገር ውጭ እየሠራችው ያለው ሃይማኖታዊ እና ማኅበራዊ አገልግሎት እያደገ እና እየተስፋፋ መምጣቱን ያመለክታል።

የዲሲና አካባቢው ሀገረ ስብከት የራሱን ይዞታ በመያዝ የዛሬ 50 ዓመት ከተቋቋመው ከኒውዮርክና አካባቢው ሀገረ ስብከት ጋር አቻ ለመሆን በመብቃቱ ቤተ ክርስቲያናችን በውጪው ዓለም የጀመረችው ሐዋርያዊ አገልግሎት በጽኑዕ መሠረት ላይ እየተገነባ ለመሆኑ አስተማማኝ እማኝ ሊሆን ችሏል። መንበረ ጵጵስናው አስፈላጊውን ሕጋዊ ፎርማሊቲ ካሟላ በሁዋላ በቅርቡ አገልግሎት መስጠት እንደሚጀምር የሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስና የዚህ አኩሪ ተግባር አንቀሳቃሽ ብፁዕ አቡነ አብርሃም ገልጸዋል።

 

Home| Feedback| Webmaster
EOTC-DC Diocese., All Rights Reserved